Quantcast
Channel: , Author at Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

ወዴት እየሄድን ነው? (ሉሉ ከበደ)

$
0
0

ከሉሉ ከበደ

የተሻለ ቀን መጣ ፤ ወይም ሊመጣ ነው ብለን ያለፈ ሁለት አመት በፊት ነፍሳችን በደስታ ነዳ ፤ ሲሞቀን ሰንብተን ፤ ብዙም ሳንቆይ ነበር የመጀመሪያው ዙር ዘር የማጽዳት ፕሮግራም ጌዴዎ ላይ የተጀመረው ። የኦሮሞ ጽንፈኞች በመንግስት ያስተዳደር ስራ ላይ ካሉ የኦሮሞ ተወላጆች ጋር በመተባበር አንድ ሚሊዮን ጌዴዎችን ከሚኖሩበት መሬት ላይ አፈናቀሏቸው ፡፡ የሚያርዱትን አረዱ ፤ የሚቃጠለውን አቃጠሉ ፤ የሚሰቀለውን ሰቀሉ ፤ ህዝቡም ሙልጭ ብሎ ሸሸ ፡፡ መንግስት የሚባለው ሰምቶ እንዳልሰማ ነበር ዝም ያለው ። ጃዋርና ቡድኑ ሊያደርጉ ያቀዱትን ነገር ደብቀውን አያውቁም ። በነጻነት መርዛቸውን የሚረጩበት ቴሌቪዥን ( OMN ) መሀል አዲስ አበባ ውስጥ ከፍተው ፤ ኦሮሞን በሌላው ህዝብ ላይ የማነሳሳቱን ስራ በሚያስደነግጥ የሀሰት ታሪክ ፈጠራ እየታገዙ ፤ እረደው ፤ግደለው፤ አቃጥለው ሲሉ ሊያቆማቸው የፈለገ መንግስት አልነበረም ፡፡ ቀጠለና አዲስ አበባ ዙሪያ ቡራዩ ላይ ዘር ማጽዳቱ ተፋፋመ ፡፡ ቡራዩ ላይ ያሁሉ ሰው በገጀራ ሲጨፈጨፍ ዶክተር አብይ የማያዳግም እርምጃ ወስዶ ለዘላለም ያቆመዋል ብለን ጠበቅን ፡፡ አልሰማም አላየም ፡፡ ቀጠለና በለገጣፎ ተመሳሳይ ድርጊት ተደገመ ፡፡ ማንም ምንም ያደረጋቸው የለም ጨፍጫፊዎቹ የጃቸውን ደም አደራርቀው ለሌላ ዙር ጥሪ እስኪደርሳችው እየተዝናኑ እረፍት አደረጉ ፡፡

መንግስት የሚያዘው ጦር ሰራዊት እያለው ፤ የሚያዘው ፖሊስ እያለው ፤ ፍርድ ቤት ዳኞች እያሉት ፤ ሰዉን በእጃችው ያረዱት ልጆች እዚሁ በሰላም ተቀምጠው ፤ ሰብስቦ በህግ ጥላ ስር አውሎ ፤ ምርመራ አድርጎ ፤ እቅድ አውጪውንም ፤ አስፈጻሚውንም ፈጻሚውንም በቁጥጥር ስር ማዋልና የህዝቡን ሰላም መመለስ ለምን አልቻለም ? ስንል ፤ የመፈለግ ያለመፈለግ ጉዳይ እንጂ የሀይል ችግር አለመሆኑን አረጋገጥን ፡፡ እንዴት አረጋገጥን ? ምክንያት እየተፈጠረ ድርጊቱን በቀላሉ መደጋገም መደበኛ ስራ ሆነ ።

ጃዋር የሚባለው ባለጌ ፤ ታዳጊ ሂትለር “ተከበብኩ ” ብሎ እንደከብት ለሚነዳው መንጋ መልክት በመላኩ ፤ ገጀራና ድንጋይ ፤ አጠና የታጠቁ ወጣቶች እንደልባቸው እየተንቀሳቀሱ ለማሰብ በሚክብድ ችካኔ ከሰማንያ ስድስት ሰው በላይ ጨፈጨፉ ፡፡ ያቆማቸው አልነበረም ፡፡ ስለ ተጨፈጨፉት ድሆች የተጨነቀ ባለስልጣን አልነበረም ፡፡ ዶክተር አብይ ሀረር ሄዶ ኦሮሞዎችን ብቻ ሰብስቦ ” ጃዋርን እንወደዋለን ፤ እንጠብቀዋለን ፤ አንነካውም ፤ አይዟችሁ ፤ አብረን እንሰራለን ” ብሎ ተመለሰ ፡፡

ከዚያ በኋላ ደግሞ አስራ ሰባት የአማራ ልጆች አድገው ያልጨረሱ ልጃገረዶችና አንድ ወንድ ልጅ ፤ ጠዋት ማታ እናት አባት አይን አይናቸውን እያየን አደጉልኝ የምንላቸውን ልጆች ወለጋ ከደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ” አማራ ስለሆናችሁ ሂዱልን ” ብለዋቸው ፤ ተሰብስበው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ ፤ መንገድ ጠብቀው የኦሮሞ ጽንፈኞች አፍነዋቸው ወዴት እንዳደረሷቸው እስካሁን ያወቅነው ነገር የለም ፡፡ መንግስት የሚባለውም ወገን እንኳን ልጆቹን ሊያስመልስ ወላጆቻቸውን ትንፍሽ ትሉና ብሎ ማሰርና ማንገላታት ይዟል ፡፡

ይህን ሁሉ ወንጀል እየሰሩ በሰላምና በድሎት እዚችው ሀገር ውስጥ በመኖር ላይ ያሉ ሰዎች ፤ አሁን ደግሞ እጅግ ከፍ ያለ ታሪክ እንስራ ብለው ፤ ተወዳጁን አርቲስት ሀጫሉን ጭዳ አደረጉት ፡፡ ከሁለት አመት በላይ ያሻቸውን ሲያደርጉ ፤ ያሻችውን ሲናገሩ ፤ ያበረታታቸው እንጂ ያስደነገጣችው ስለሌለ ፤ ተራው የነሱ መሆኑን ራሳቸው መንግስት መሆናቸውን አመኑ ፡፡ እነጃዋር የሚሉት ” የኦሮሞን ወጣት አስተባብረን አሳምጸን ለውጡን ያመጣነው እኛ ነንና ፤ እኛው ሀገሪቱን መግዛት አለብን ” ነው ፡፡ ሀያሰባት አመት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን ስር እት በመታገል ያሳለፈው ጊዜ ፤ የገበረው ደምና ንብረት ለነሱ ምንም አይደለም ፡፡ በሀጫሉ የቀብር ስነስራት ላይ እንዲገኝ እናደርጋለን ያሉትን መቶ ሺህ ጽንፈኛ አስታጥቀውና አስተባብረው በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ ሊያንቀሳቅሱት የነበረውን ታላቅ የዘር ጭፍጨፋ ብሎም መንግስቱን የመቆጣጠር እቅድ መክሸፉ እግዚ አብሄር ጣልቃ ቢገባ ነው ፡፡

እዚች ሰአት ላይ መንግስትም ለሰራው ብልህነት የተሞላው ስራ ሊመሰገን ይገባል ፡፡ ይሁንና በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች የኦሮሚያ ክልል ነው በተባለ ክፍል በቀላል ቁጥር የማይገመት የሰው ህይወት፤ ሀብትና ንብረት በታሪክ ባልታየ የጭካኔ አይነት እየተጨፈጨፈ ነው ፡፡ ስምንት ቤተሰብ እንዳለ ተጨፍጭፎ በእሳት ሲቃጠል ማየት በኢትዮጵያ ታሪክስ ነበረ ?

ግን መንግስት ከንግዲህ በኢትዮጵያ ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይደገም ፤ እንዳናይ ያደርጋል ? አስፈላጊውን በጀትና የሰው ሀይል መድቦና አሰማርቶ ፤ እነዚህን ወንጀለኞች እስከመጨረሻው አድኖ ፤ ለሰሯት ስራ ተመጣጣኙን ቅጣት እየሰጠ በማሳየት ፤ ሌሎች እየተዘጋጁ ያሉትን ሊያመክናቸው ይችላል ? ለዚህ ውድቀት የዳረገንን ሀያ ስምንት ፤ ሀያዘጠኝ አመት የተረጨ የዘረኝነት መርዝ ለማጥፋት ስራ ይጀምራል ? መጀመሪያ ህገመንግስቱን ያጸዳል ? ህዝቡን ወደ ጤናማ አስተሳሰብ ለመመለስ የታሪክና የአብሮ ነትን ትምህርት በዘመቻ መልክ መስጠት ይጀምራል ? ህጻናት በትምህርት ቤት መርዝ እየተጋቱ ፤ ጥላቻ እየተጋቱ እንዲያድጉ የተደረገበትን የፈጠራ ታሪክ በመጽሀፍ እየተጠረዘ የሚቀርብበትን ስርአተ ትምህርት ዛሬ ነገ ሳይል ይቀይራል ? በዘር የተከለለውን ህዝብ ነጻ ለማውጣት ክልልሎችን ያፈርሳል ? የዚህ ሁሉ በሽታ ጠንሳሽና ጠማቂ እንደሰው ሳይሆን እስካሁንም ድረስ እንደአውሬ በማሰብ ላይ ያሉትን የትግሬ ነጻ አውጭ ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሎ ህዝቡን ነጻ ያወጣል ? በአምሳላቸው የፈጠሯቸውን የኦሮሞ ጽንፈኛ ነጻ አውጭ ነን ብለው ሀገር በማመስ ላይ ያሉትን ዘረኞች በቁጥጥር ስር አውሎ ህዝቡን ነጻ ያወጣል ?

” ጦርነት እንከፍታለን ፤ በጉልበታችን የጀመርናትን ሀገር ጨርሰን እናፈርሳታለን ፤ የራሳችንን መንግስት እናቆማለን” ቢሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ “ተነስ! ሀገርህን አድን ! ” የምትል የአምስት ደቂቃ ጥሪ ትበቃዋለች ከልቡ ከተነሳ መሪ ጎን ለመቆም ፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ እንደዚያ አይነት መሪ ይወጣዋል ?

ይህ መንግስት እነዚህን ጥቂት ነገሮች ቢያደርግ እንድናለን ፡፡ ይህ ካልሆነ እስካሁን የተፈጸመውን የዘር ማጽዳት ስራ በየጊዜው ጠብቁ ፡፡ እግዚአብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይታደግ ፡፡



Source link

The post ወዴት እየሄድን ነው? (ሉሉ ከበደ) appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

Trending Articles