Quantcast
Channel: , Author at Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

“ከሱዳን ጋር ግጭት እንዲኖረን አድርገው የራሳቸውን ዓላማ ለማሳካት የሚፈልጉ ኀይሎች ገብተዋል”የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

$
0
0

“ከሱዳን ጋር ግጭት እንዲኖረን አድርገው የራሳቸውን ዓላማ ለማሳካት የሚፈልጉ ኀይሎች ገብተዋል” የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ባሕር ዳር፡ ጥር 12/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከኦስትሪያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በነበራቸው ውይይት በሀገራቱ ግንኙነት ዙሪያ፣ ስለተወሰደው የህግ ማስከበር ዘመቻና የሰብዓዊ አገልግሎት ሥራዎችና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲሁም በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ጠቅሰዋል።

አቶ ደመቀ ከአዲሱ የቻይና አምባሳደር ጋርም በሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂካዊ ግንኙነቶች ላይ እንደተወያዩ አንስተዋል።

አምባሳደር ዲና በኢትዮጵያና ሱዳን ግንኙነት ዙሪያ በሰጡት መግለጫም ሀገራቱ እንደህዝብ ጥብቅ ትስስር ያላቸው ናቸው ብለዋል።

ሱዳን እንድትረጋጋና የፖለቲካ ኀይሎች አንድ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ኢትዮጵያ የጎላ ሚና ነበራት፤ ነገር ግን ከሱዳን ጋር ግጭት እንዲኖረን አድርገው የራሳቸውን ዓላማ ለማሳካት የሚፈልጉ ኀይሎች ገብተዋል ነው ያሉት።

በሕግ ማስከበር ርምጃው ወቅት አካባቢው እንዳይረበሽ እንድትጠብቅና ወንጀለኞች በሱዳን እንዳይወጡ ከሃገሪቱ መንግሥት ጋር ተነጋግረናል፤ ሆኖም እነሱ በጀርባ ወደግዛታችን ገብተው ከጠበቅነውና ከተነጋገርነው በተቃራኒ የሆነ ድርጊት ፈፅመውብናል፤ ይህም የሱዳን ሕዝብ ፍላጎት አይደለም የበለጠም ይጎዳዋል ብለዋል። አሁንም ያለማንም ጣልቃገብነት ወደነበሩበት ተመልሰው ድርድር እንዲካሄድ ጥሪ እያቀረብን ነው፤ ለዘላቂ ሰላሙም የሚጠቅመው ይህ ነው ብለዋል ቃል ዐቀባዩ ።

ኢትዮጵያ የውስጥ ሰላሟን ለማስከበር በቂ ኀይል ያላት ሀገር ነች፣ ጦርነት ለመጋበዝ ፍላጎት የነበራቸው ጠላቶች ወደ ኤርትራ ትንኮሳ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም፤ የሕግ ማስከበር ዘመቻውን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቃችን ጠላቶቻችንን ለመነገድ ያሰቡ ኀይሎችን አስከፍቷል ብለዋል።

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ የሦስትዮሽ ድርድር ተደርጓል፤ ሱዳኖች በግድቡ ከፍተኛ ተጠቃሚ መሆናቸውን የተቋቋመው ዓለምአቀፍ የባለሙያዎች ቡድን በሰጠው ምክረ ሀሳብ ገልጿል፤ ይህንን የሱዳን መሪዎችም እንደሚያውቁ አምባሳደር ዲና ተናግረዋል። ጥያቄ ያነሱት የግድቡ ደኀንነት ላይ ነበር በቂ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፤ አሁን በድርድሩ ወጣ ገባ የሚሉት የሌሎች ሀሳብ ወኪል ሆነው ነው፤ የሱዳን ሕዝብ ግድቡ ምንያህል እንደሚጠቅመው ያውቃል፤ መሪዎችም ይህንን እንዲረዱ እናስገነዝባለን ብለዋል።

ዘጋቢ : – ዘመኑ ታደለ-ከአዲስ አበባ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

The post “ከሱዳን ጋር ግጭት እንዲኖረን አድርገው የራሳቸውን ዓላማ ለማሳካት የሚፈልጉ ኀይሎች ገብተዋል” የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

Trending Articles