Quantcast
Channel: , Author at Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

“የዘንድሮው የጥምቀት በዓል ከሀገር ውስጥ ጎብኝዎች ከፍተኛ ገቢ ማግኘት እንደሚቻል ትምህርት የተወሰደበት ነው”የጎንደር ከተማ አስተዳደር

$
0
0

“የዘንድሮው የጥምቀት በዓል ከሀገር ውስጥ ጎብኝዎች ከፍተኛ ገቢ ማግኘት እንደሚቻል ትምህርት የተወሰደበት ነው” የጎንደር ከተማ አስተዳደር

ባሕር ዳር፡ ጥር 12/2013 ዓ.ም (አብመድ) በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ከማይደሰሱ ቅርሶች መዝገብ መስፈር የቻለው የጥምቀት በዓል በድምቀት ተከብሯል፡፡

ከሃይማኖታዊ ፋይዳው በተጨማሪ በቱሪዝም ዘርፍ የገቢ ምንጭ ከሆነው የጥምቀት በዓል ገቢ ማግኘት እንዲቻልም የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከአጋር አካላት ጋር ዝግጅት በማድረግ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅና ኢኮኖሚዊ ጥቅም እንዲያስገኝ ማድረግ ተችሏል፡፡

በከተማዋ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ነዋሪዎችም እንግዶችን ተቀብለው ከማስተናገድ ባለፈ በሚሰጡት አገልግሎት ከሌላው ጊዜ በበለጠ ገቢ ማግኘታቸውን ነው የተናገሩት፡፡

የባህላዊ ልብሶችን በመሸጥ የምትተዳደረው ህይወቴ ፋሲል የአካባቢውን ባህል የሚገልጹ አልባሳትን ለገበያ በማቅረብ በብዛት በመሸጥ ተጠቃሚ መሆኗን ገልፃለች፡፡

ሌላው አስተያቱን የሰጠው ወጣት ቶማስ ሙሉየ ለጎብኝወች ፈረስ በማስጋለብና ታሪካዊ ቦታዎችን በማስጎብኘት የሚተዳደር ሲሆን የጥምቀት በዓልን ለማክበር ወደ ጎንደር ለመጡ የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች በሥራው አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ ገቢ ማግኘት እንደቻለ ተናግሯል፡፡

ጥምቀት ለኛ ሀይማኖታዊ በዓላችን ብቻ ሳይሆን የገቢ ምንጫችንም ነው ብሏል ቶማስ፡፡

በከተማዋ ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚሰጡ ሆቴሎች፣ ሱቆች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ አሽከርካሪዎች ለበዓሉ ታደሚዎች በሰጡት አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የባህል ቱሪዝምና ስፓርት መምሪያ የባህል እሴቶች እና ኢንዱሰትሪ ልማት ቡድን መሪ ልዕልና ገብረመስቀል ለዘንድሮው የጥምቀት በዓል በጎንደር የነበረው ዝግጅትና በስኬት መጠናቅ አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ የጥምቀት በዓል የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃት አግዟል ነው ያሉት፡፡

በዘንድሮው የጥምቀት በዓል ከተማዋን ለማስተዋወቅና ገቢም ለማግኘት ዝግጅት ተደርጎ በዓሉ በስኬት ተጠናቋል ብለዋል አቶ ልዕልና፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የውጭ ሀገር ጎብኝዎችን ቁጥር የቀነሰ ቢሆንም በርካታ የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች ወደ ጎንደር በመምጣት በዓሉን መታደማቸው ከሀገር ውስጥ ጎብኝዎች የተሻለ ገቢ ማግኘት እንደሚቻል ትምህርት የተወሰደበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

The post “የዘንድሮው የጥምቀት በዓል ከሀገር ውስጥ ጎብኝዎች ከፍተኛ ገቢ ማግኘት እንደሚቻል ትምህርት የተወሰደበት ነው” የጎንደር ከተማ አስተዳደር appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

Trending Articles