Quantcast
Channel: , Author at Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

ባለሃብቶች ለገበታ ለሃገር የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኝ ብሔራዊ ሐብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

$
0
0

ባለሃብቶች ለገበታ ለሃገር የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኝ ብሔራዊ ሐብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር፡ ጥር 12/2013 ዓ.ም (አብመድ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው ብሔራዊ ኮሚቴ አባልና የባለሃብቶች አስተባባሪ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ እንደተናገሩት ኮይሻ፣ ጎርጎራና ወንጪ ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር የሃብት ማሰባሰብ መርኃ ግብር እየተከናወነ ነው።

በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚለሙት ሦስቱ ፕሮጀክቶች የክልሎችን፣ የከተማና የቱሪዝም ልማትን ለማስፋት ታሳቢ ያደረጉ ናቸው።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የነዚህን ፕሮጀክቶች ሥራ ለማስጀመር እየተካሄደ ባለው የሃብት ማሰባሰብ ተግባር በሁሉም ዘርፍ ያለው የንግድ ማኅበረሰብ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

የግሉ ዘርፍ ከጅምሩ ያሳየው ምላሽ አዎንታዊ መሆኑን ያወሱት አምባሳደር ምስጋኑ በሸገር ፕሮጀክቶች የነበረው ተሳትፎና ድጋፍ ለገበታ ለሃገርም ተጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል።

በቀጣዩ ሣምንት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የማጠቃለያ የእራት መርኃ ግብር እንደሚካሄድም አስታውቀዋል።

በመርኃ ግብሩ ለመሳተፍ በቪአይፒ 5 ሚሊዮን ብር በቪቪአይፒ ደግሞ 10 ሚሊዮን ብር ሲሆን በርካታ ባለሃብቶች ገንዘቡን ገቢ እያደረጉና ቃል እየገቡም ነው ብለዋል።

ቃል የገቡ ባለሃብቶች በቀሪዎቹ ቀናት ቃላቸውን በመፈጸም በመርኃ ግብሩ ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሮጀክቶቹ ዓለም አቀፍ ቱሪዝምና ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ የሥራ ዕድል በመፍጠርና ለባለሃብቱም ያላቸውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታም አብራርተዋል።

አዳዲስ ሃብት በመፍጠርና የንግድ እሳቤዎችን በማምጣት ለባለሃብቶች ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የመሳተፍ ዕድል ይዘው ይመጣሉ ብለዋል።

ባለሃብቶች በሀገራዊ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በሚሊዮኖች በሚቆጠር ገንዘብ አስተዋጽኦ በማድረግ መሳተፋቸው አዲስ ጅማሬ በመሆኑ የበለጠ እንዲሳተፉ ምቹ ሁኔታዎችን መዘርጋት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

ፕሮጀክቶቹ ኢትዮጵያን በትብብር በማልማት አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ የመፍጠር እሳቤን ለማሳካት ተምሳሌት መሆናቸውን አምባሳደር ምስጋኑ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአዲስ አበባ የብሔራዊ ቤተ-መንግሥት፣ ወዳጅነት ፓርክ፣ እንጦጦና መስቀል አደባባይ ፕሮጀክቶች በስኬት መጠናቀቃቸው ለከተማዋና ለሀገሪቷም አዳዲስ ዕድሎች፣ ልምዶች፣ የንግድ ሃሳቦችና እሴቶችን ይዘው መምጣታቸውን አውስተዋል።

ፕሮጀክቶቹ አንድነትን፣ ብሔራዊ መግባባትን፣ የጋራ ልማትና አብሮነትን የሚያስተሳስሩ በመሆናቸው ለስኬታማነታቸው ሁሉም በሚችለው ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

The post ባለሃብቶች ለገበታ ለሃገር የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኝ ብሔራዊ ሐብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡ appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

Trending Articles