አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሄዳል።
በስብሰባውም የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ምክር ቤቱ ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም በቤኒሻንጉል ጉምዝ በመተከል ዞን እና በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ ከተወያየ በኋላ በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ውሳኔ ሀሳቡን ያጸድቃል።
የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል የዳኝነት አስተዳደር ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን ያጸድቃል።
የኢትዮዽያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የካፒታል ገበያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል።
በኢትዮጵያ መንግስት እና በኡጋንዳ ሪፐብሊክ መካከል የተደረገውን በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ መንግስት እና በኡጋንዳ ሪፐብሊክ መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትሕ ትብብር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ ይጠበቃል።
በኢትዮጵያ መንግስት እና በደቡብ አፍሪካ መንግስት መካከል የዲፕሎማቲክ ወይም ሰርቪስ ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል።
በኢትዮጵያ መንግስት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውል የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 32(2)ን በጊዚያዊነት ስለማገድ ያቀረበውን ማሻሻያ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ከምክርቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
The post 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሄዳል appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.