Quantcast
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

ከአቶ ድንቁ ጀርባ ያሉትስ? –ግርማ ካሳ

Image may be NSFW.
Clik here to view.
የዋልታ ምርመራን ዘገባ ሳላዳምጥ ብዙ አስተያየት መስጠት አልፈለኩም ነበር፡፡ አሁን አደመጥኩት፡፡

አንድ ወቅት ከሶማሌ ክልል ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜግች፣ በዋናነት ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ሲፈናቀሉ ተፈናቃዮችን ለማቋቋም እንቅስቃሴ ሲደረግ ብዙ እናበረታታ ነበር፡፡ አቶ ድንቁ፣ ያኔ ገንዘብ እንደሚለግሱ በተናገሩ ጊዜ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ብዬ እውቅና ሰጥቼ እንዳመሰገንኳቸው አስታወሳለሁ፡፡

አሁን ስለ እኝህ ሰው ዋልታ ሰፊ ዘገባ አቅርቧል፡፡ በዘገባው የቀረበው ስህተት ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡በተለይም ገበሬዎች የሚናገሩትን ስሰማ ውስጤ በጣም ነው ያዘነው፡፡

ሆኖም ግን በዚህ መልኩ ፍርድ ቤትን በመቅደም ዜጎችን ራሳቸውን መመከት በማይችሉበት ሁኔታ በሜዲያ መክሰስ ተገቢ አይመስለኝም፡፡

እርግጥ ነው ዋልታ የሶደሬ ሪዞርት ዳይሬክተሩን ለማነጋገርና በዚያኛው ሳይድ ያለውን ለማቅረብ ሞክሯል፡፡ ዳይሬክተሩ ለመቅረብ ፍቃደኛ አልሆኑም እንጂ፡፡ ሆኖም አቶ ድንቁን ሆነ የአቶ ድንቁ ድርጅት ተወካዮች፣ የሕግ ሰዎችን ሆነ አቶ ድንቁን ራሳቸው ምን ያህል እነርሱም የሚሉትን ለመስማት ሞከሩ የሚለውን ብንጠይቅ ምን አልባት የሚሰጠን መልስ አጥጋቢ ላይሆን ይችላል፡፡አቶ ድንቁ በአሁኑ ወቅት አገር ቤት እንደሌሉ ነው የሚገለጸው፡፡

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያይዘ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ማቅረብ እፈልጋለሁ

አንደኛ አቶ ድንቁ ሰሩ የተባለውን ወንጀል እንደሰሩ እየታወቀ ለምን ከአገር እንዲወጡ ተደረገ ?

ሁለተኛ አቶ ድንቁ ከአቶ ለማ መገርሳ፣ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬን ከመሳሰሉት ጋር ከበርካታ የኦሮሞ ክልልና የኦህዴድ ሃላፊዎች ጋር ቅርበት ያላቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡ እኝህ ሰው አደረጉት የተባለው፣ ያለ ኦሮሞ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ያደርጋሉ ተብሎ አይታሰቡ፡፡ እኝህ ሰው በየትኞቹ የኦህዴድ ትከሻዎች ላይ ሆነው ነበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ?

ሶስተኛ አሁን አቶ ድንቁ አደረጉት እንደተባለው፣ በትንሽ ገንዘብ ገበሬዎችን አታለው፣ ከመሬቶቻቸው ያፈናቀሉ እጅግ በጥም በርካታ የኦሮሞ ክልል ባለስልጣናት አሉ፡፡ በተለይም በአዲስ አበበ ዙሪያ፣ በሰበታ፣ በሱሉልታ፣ በለገጣፎ፣ በዱከም፣ በሞጆ፣ በአዳማ …በርካታ ገበሬዎች በኦሮሞ ክልል ሃላፊዎች ተፈናቅለዋል፡፡ እነዚህ ቦታዎች የተሰሩ ግፎች ቢመረመሩ አሁን አቶ ድንቁ አደረጉት ከተባለው የማይተናነስ ግፎች አልተፈጸሙምን ? ቀላል ምሳሌ አሁን የአዲስ አበባ ከንቲባ ከንቲባ የሆነው ታከለ ኡማ የሰበታና የሱሉልታ ከንቲባ ሆኖ ሰርቷል፡፡ ያኔ ገበሬዎች አላፈናቀለም? ሲያፈናቅልም በቂ ካሳ ከፍሏቸው ነውን?

እንግዲህ ሕግ ዥንጉርጉር መሆን የለባትም፡፡ ሁሉም በሕግ ፊት እኩል መሆን አለባቸው፡፡ ልክ እንደ አቶ ድንቁም በርካታ የኦህዴድ ሃላፊዎች መመርመር ይኖርባቸዋል ባይ ነኝ፡፡ እኛን ሲደገፉ ዝም ማለት ወይንም ወንጀልን መደበቅ፣ እኛ ሲቃወሙ ግን መከሰስ ፣ በኔ እያታ ግብዝነት፣ አርደባይነትና ኢፍትሃዊነት ነው፡፡

ድንቁ ደያስ የኦሮሚያ ሜይቴክ ወይስ የፖለቲካ ሰለባ?

ድንቁ ደያስ የኦሮሚያ ሜይቴክ ወይስ የፖለቲካ ሰለባ?“Mehal Meda” is an Amharic phrase, which, in essence, means a “central venue”. This channel is dedicated to provide a platform where various perspectives are reflected on current, past, and future social, political, scientific, religious, economic, health, legal, historical, and cultural events and phenomena that affect East Africa; especially, our beloved homeland, Ethiopia, and her twin, sovereign and independent sister-nation, Eritrea.Mehal Meda encourages civil, respectful, positive discourses and discussions as it serves as a venue for peoples of Ethiopian and Eritrean origins to share their opinions, frustrations, concerns, expectations, life-experiences, aspirations, hopes, and dreams.Mehal Meda does not offer any professional advise, nor does it make claims of expertise in any general or particular area.Disclaimer: Mehal Meda often refers to and uses materials and clips from various media, including, audio and videos of interviews, news, events, documents, discussions, printed materials, etc. of various contents from other sources, which may be copyrighted; such uses are for the sake of reference only, and in such materials, the credit goes to the copyright owner. Mehal Meda does not intend on infringing any entity’s intellectual property. In instances where such copyrighted materials are used without them being specifically authorized by the copyright owner, the use of such copyrighted materials from other sources constitute a fair use as provided in Section 107 of the U.S. Copyright Law and as provided in title 17 U.S.C. Section 107. Mehal Meda is a non-for-profit channel and media.Any discussions points, thoughts, views, assertions, perspectives, and opinions expressed by viewers and readers, be it in writing, graphically, vocally, or in any other way, do not necessarily reflect the opinions of Mehal Meda and/or its management; therefore Mehal Meda and/or its management are not responsible for contents that other individuals and entities may express, publish, post, voice, upload, distribute or transmit on Mehal Meda’s YouTube channel and/or its website and comment sections.

Posted by Mehal Media መሀል ሚዲያ on Wednesday, June 10, 2020

The post ከአቶ ድንቁ ጀርባ ያሉትስ? – ግርማ ካሳ appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

Trending Articles