Quantcast
Channel: , Author at Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

“መፈንቅለ መንግሥት እንድናደርግ ተጠይቀን እምቢ ብለናል፡፡”–የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሳሞራ የኑስ

$
0
0

ጀነራል ሳሞራ የኑስ ከአውሎ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ “ኢህአዴጎች በ2010 ጥልቅ ታህድሶ አድርገው የአመራር ለውጥ እያደረጉ ባለበት ወቅት ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት እንዲያደርግ የሚጠይቁ መአት ሠዎች ነበሩ” ብለዋል፡፡ ሠዎቹ እነማን እንደነበሩ ግን በግልፅ አልተናገሩም፡፡

“የወታደር ስራ ሀገር መጠበቅ በመሆኑ ፖለቲካው ውሥጥ አልገባንም ያሉት ጀነራል ሳሞራ፤ መሪ በተለዋወጠ ቁጥር ጥይት መጮህ ስለሌለበት ኢህአዴጎች የወሰኑት ውሳኔ ላይ ጣልቃ አልገባንም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሠራዋቱ የበላይ አመራሮች በከባድ ሙስና ይታማሉ ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄም “የሠራዊቱን ስም ለማጥፋት የሚደረግ ዘመቻ ነው እንጂ እውነት አይደለም፡፡ ቦሌ የሳሞራ ነው እየተባለ ብዙ ተወርቷል፡፡ ይህ ግን ውሸት ነው፡፡ ሠራዊቱ ሙስናን የሚከላከልበት የራሱ አሰራር አለው፡፡ ፀረ ሙሥናም ሀብታችንን መርምሯል፡፡ አሁንም እኔ በግሌ ሀብቴን ለማስመርመር ዝግጁ ነኝ” ብለዋል፡፡

የመከላከያ ወታደሮች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በነበሩ ተቃውሞዎች ዜጎችን ስለመግደሉ የተጠየቁት ጀነራል ሳሞራ የኑስ “እንደውም ሠራዊቱ ሲገደል ነበር፡፡ ሠራዊቱ እየሞተ ነበር ሠላም ሲያስከብር የነበረው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ አባል ሆነዋል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም “እኔ የብልፅግና ፓርቲ አባል ለመሆን መሥፈርቱን አላውቅም፡፡ ባውቅም መሥፈርቱን የማሟላ አይመሥለኝም፡፡ እንደ ዜጋ ምክር ስጠየቅ ግን ለህዝብ በሚጠቅም መልኩ ሀሣብ መስጠቴን እቀጥላለው፡፡” ብለዋል፡፡

ነጋሪት

The post “መፈንቅለ መንግሥት እንድናደርግ ተጠይቀን እምቢ ብለናል፡፡” – የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሳሞራ የኑስ appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

Trending Articles