Quantcast
Channel: , Author at Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

በአምባሰል ወረዳ በ64 ሚሊየን ብር ወጭ የተገነባ የመስኖ ፕሮጀክት ተመረቀ

$
0
0
አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ በ64 ሚሊየን ብር ወጭ የተገነባ የላይኛው ሚሌ መስኖ ፕሮጀክት ተመርቆ አገልግሎት ጀመረ።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገርና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ተገኝተዋል።
የክልሉ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኅላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው በወቅቱ እንደገለጹት÷የመስኖ ፕሮጀክቱ 6 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የውሀ መውረጃ ቦይ የተገነባለትና 350 ሄክታር መሬት የማልት አቅም ያለው ነው።
ፕሮጀክቱ 750 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
በዛሬው እለት የተመረቀው ፕሮጀክቱ በመስኖ ልማት ስልጠና በተሰጣቸው አርሶ አደሮች ስራ እንዲጀምር መደረጉን አስታውቀዋል።
በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት 2 ሺህ 955 ሄክታር መሬት ማልማት የሚችሉ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑንም ኅላፊው ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገርና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ዛሬ ከቀትር በኋላም የይስማ ንጉስ ሙዚየምና 40 ሜትር ርዝመት ያለውን የአጅማ ድልድይ ይመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በአምባሰል ወረዳ በ64 ሚሊየን ብር ወጭ የተገነባ የመስኖ ፕሮጀክት ተመረቀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.



Source link

The post በአምባሰል ወረዳ በ64 ሚሊየን ብር ወጭ የተገነባ የመስኖ ፕሮጀክት ተመረቀ appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

Trending Articles