
መጪው አገራዊ ምርጫው ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄድ ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደርች ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው አስገንዝበዋል።
ባሕር ዳር፡ ጥር 07/2013 ዓ.ም (አብመድ) መጪው አገራዊ ምርጫው ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄድ ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደርች ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው አስገንዝበዋል።
በዘንድሮው 6ኛ አገራዊ ምርጫ የፀጥታና ደኀንነት ችግር እንዳያጋጥም ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ። ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በምርጫው ዕቅድ፣ አገራዊ የደኀንነት ስጋቶች እንዲሁም የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተወያይተዋል።
የምርጫውን ደኀንነት ለማስጠበቅ በአገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው ግብረሃይል ቀደም ሲል ባካሄደው ውይይት ክልሎች የአካባቢያቸውን ችግሮች ለይተው የፀጥታ ዕቅድ እንዲያወጡ አቅጣጫ አስቀምጧል።
በዚሁ መሰረት ክልሎቹ ያወጡት ዝርዝር ዕቅድ ዛሬ ተገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ ተሰጥቶበታል።
የምርጫውን ደኀንነት የሚፈታተኑ ችግሮችን ለይቶ ከፀጥታና ከሕግ አፈፃፀም አኳያ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ ላይ ያተኮረው ውይይት ምርጫውን ሠላማዊ ማድረግ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ መክሯል።
የምርጫ ዕቅድ ሪፖርት ካቀረቡ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አዲስ አበባ፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ሀረሪ ክልሎች የተሻለ ዕቅድ፣ ይዘትና ነባራዊ ሁኔታን ተንትኖ በማስቀመጥ ተሽለው ተገኝተዋል ተብሏል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ምርጫው ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄድ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
እያንዳንዱ ክልል ከፀጥታና ደኀንነት አኳያ በተገቢው ትኩረት ችግሮችን ለይቶ መስራት አለበት ነው ያሉት። ከዚህ አንፃር የምርጫውን ተሳታፊ አካላት መሰረት ያደረገ ዝርዝር ዕቅድ መውጣቱን ተናግረዋል።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በዕቅዱ የሁሉም ክልሎች ድክመትና ጥንካሬ መለየቱንና ዕቅዱ ምን ያህል ተጨባጭና ነባራዊ ሁኔታዎችን አይቷል የሚለው መገምገሙን ገልፀዋል።
ኢዜአ እንደዘገበው በዕቅዱ መሰረት ክልሎች የምርጫ አፈፃፀሙን ሠላማዊ ማድረግ አለባቸው ያሉት ሰብሳቢዋ ከዚህ አንፃር ክፍተት ያለባቸው ችግሮቹን በቶሎ እንደሚያርሙ ነው የተናገሩት።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
The post መጪው አገራዊ ምርጫው ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄድ ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደርች ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው አስገንዝበዋል። appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.