Quantcast
Channel: , Author at Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ በሴቶች እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አመርቂ መሆናቸውን ገለጹ

$
0
0

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀላባ ዞን በዌራ ወረዳ በ2ኛ ጮሮቆ ቀበሌ በሴቶች የተሰሩ ሥራዎች የመስክ ጉብኝትና የልምድ ልውውጥ ተደረገ፡፡

በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መስከረም አበበ፣ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ህይወት ኃይሉን ጨምሮ የፌደራል የስራ ሃላፊዎችና የየክል የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ መሪዎች ተገኝተዋል፡፡

የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ አብዱሰላም ሀሰን በወረዳው በሴቶች በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡

የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር መሀመድ ኑሪያ የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመቅረፍ በመንግስት በኩል በርካታ ሥራ መሰራቱን ጠቅሰው በተለይ በዌራ ወረዳ በ2ኛ ጮሮቆ ቀበሌ በሴቶች በግብርና በፍየል እርባታ ሥራ ተሰማርተው ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የፌደራል የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ እንደገለጹት በሴቶች እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች እጅግ አመርቂና በህይወታቸው ለውጥ ማምጣት የቻሉ ናቸው፡፡

ይህን ምርጥ ተሞክሮ ወደ ሌሎች ቀበሌዎች ማስፋት ይገባል ማለታቸውንም ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ምርጥ ተሞክሯቸውን ያካፈሉ ሴቶች በህይወታቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው በዚህም በሰብል ማምረት በፍየልና በዶሮ እርባታ ተሰማርተው ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!



Source link

The post የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ በሴቶች እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አመርቂ መሆናቸውን ገለጹ appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

Trending Articles