Quantcast
Channel: , Author at Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

በዳያስፖራው ተሳትፎ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል የሚያስችል ፕሮጀክት ሊተገበር ነው

$
0
0

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዳያስፖራው ተሳትፎ ከደረጃ በታች የሆኑ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል የሚያስችል ፕሮጀክት ሊተገበር መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው የዳያስፖራውን የበጎ አድራጎት ተሳትፎ ለማሳደግ በሚያስችሉ ፕሮጀክቶች ቀረፃ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲያካሂድ የቆየው አውደጥናት አጠናቋል።

በአውደጥናቱ ከደረጃ በታች ሆነው ትምህርት እየተሰጠባቸው ያሉ የዳስ ትምህርት ቤቶችን የሚያሻሽል ፕሮጀክት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለመቅረፅ ከመግባባት ላይ ተደርሷል።

የፕሮጀክት ቀረፃውን የልማት ማህበራት፣ የትምህርት ቢሮዎችና የዳያስፖራ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤቶች በጋራ በመሆን የሚያዘጋጁት ይሆናል።

በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ በተለያየ የገጠር አካባቢ 40 ያህል ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እቅድ መያዙ ተገልጿል።

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ እንድሪስ እንዳሉት ÷ዳያስፖራው በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የበጎ አድራጎት ስራዎችን አከናውኗል።

ዳያስፖራው እገዛ ከሚያደርግባቸው ዘርፎች ውስጥ የትምህርት ልማት አንዱ መሆኑን ገልፀው÷ ዘርፉን ለማገዝ የታሰቡት ፕሮጀክቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የአውደጥናቱ ተሳታፊዎች ዳያስፖራው በተለይ በትምህርትና እውቀት ሽግግር ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ ማሳደግ እንዳለበት ጠይቀዋል።

ለትምህርት ዘርፍ እንደመጀመሪያ ዙር የዳያስፖራ በጎ አድራጎት ተሳትፎ ማሳደጊያ ፕሮጀክት ቅድሚያ መሰጠቱን ተናግረዋል።

ዳያስፖራው በሌሎች የልማት ስራዎች ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ ሳይገድብ ፕሮጀክቱ እንደሚተገበርም ነው የገለጹት።

የድሬዳዋ ዳያስፖራ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አክሊለ ታጠቅ÷ ዳያስፖራው በድሬዳዋ ከተማና አካባቢው በተለያዩ የኢንቨስትመንትና የበጎአድራጎት ተግባራት እየተሳተፈ መሆኑን ተናግረዋል።

በአካባቢው አሁንም ቢሆን በዳስ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ህጻናት መኖራቸውን ጠቁመዋል።

ዳያስፖራው በትምህርት ዘርፉ ላይ የሚያደርገውን የበጎ አድራጎት ስራ በአግባቡ ለመምራት መታሰቡ መልካም ጅምር መሆኑን ገልጸዋል።

የከፋ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ይገዙ ብርሃኑ ÷ዳያስፖራው በእውቀትና ክህሎት ሽግግር ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሮጀክቱን በተቀናጀ መልኩ በፌዴራል ደረጃ ለመምራትም ስትሪንግ ኮሚቴ እንደሚቋቋም ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Source link

The post በዳያስፖራው ተሳትፎ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል የሚያስችል ፕሮጀክት ሊተገበር ነው appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

Trending Articles