Quantcast
Channel: , Author at Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

አምባሳደር ይበልጣል በሱዳን ከኖርዌይ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

$
0
0

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን የኖርዌይ አምባሳደር ቴሬዝ ሎክን ህዜል ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደሩ ከአምባሳደር ቴሬዝ ሎክን ህዜል ጋር በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።

ከዚህ ጋር በተያይዘ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትን፣ የሰብዓዊ መብት አያያዝን እንዲሁም የኢትዮጵያንና የሱዳንን ድንበር እና በቀጠናው የሚስተዋሉ ጉዳዮችን በተመለከተ አምባሳደሯ ላነሷቸው ጥያቄዎች ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በዚሁ መሰረት በትግራይ ክልል ከሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትና ሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር በተያያዘ የሚነሱ የተዛቡ አስተያየቶች መንግስት በአካባቢው ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በሚያደርገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ በመሆናቸው ለትግራይ ሕዝብም ሆነ በአጠቃለይ ለኢትዮጵያዊያን እቆረቆራለሁ የሚል አካል ካለ የመንግስትን ጥረት መደገፍ እንደሚገባ አምባሳደር ይበልጣል አስረድተዋል፡፡

አምባሳደሩ በማያያዝም የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ችግር የሚፈቱባቸው መንገዶች በግልፅ በስምምነት የተቀመጡ በመሆኑ በዚሁ መሰረት ዘላቂ ሰላም በሁለቱ ሀገራት እና በቀጠናው በሚያመጣ መልኩ መፍታት እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ከሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!



Source link

The post አምባሳደር ይበልጣል በሱዳን ከኖርዌይ አምባሳደር ጋር ተወያዩ appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

Trending Articles