Quantcast
Channel: , Author at Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የትምህርት ተቋማትን ደረጃ ወደ 50 በመቶ ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

$
0
0

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የትምህርት ተቋማትን ደረጃ ወደ 50 በመቶ ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

ባሕር ዳር፡ ጥር 14/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ከጎንደርና አካባቢው የአልማ ኮርፖሬት አባላት ጋር እየተወያየ ነው። ምክክሩ አልማ ከ2012 እስከ 2014 ዓ.ም በሕዝባዊ ተሳትፎ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን በመገምገም ለቀሪዎቹ ስኬት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው ተብሏል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሞላ መልካሙ አልማ የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመቅረፍና የትምህርት ተቋማትን ደረጃ ለማሻሻል ጥረት እያደረገ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የማኅበሩ አባላትና የአካባቢው ተወላጆች እያደረጉት ላለው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል። ከንቲባው በጎንደር ከተማ ያለውን የትምህርት ተቋማት ደረጃ ከ3 ነጥብ 7 በመቶ ወደ 50 በመቶ ለማሳደግ ታልሞ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ለስኬታማነቱ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መልዕክ አስተላልፈዋል። አልማ ከ2012 ዓ.ም እስከ 2014 ዓ.ም ባሉት ሦስት ዓመታት የቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማትን ደረጃ ለማሻሻል 21 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል ተብሏል፡፡

በማዕከላዊ፣ በምዕራብና በሰሜን ጎንደር ዞኖች እምዲሁም በጎንደር ከተማ አስተዳደር 1 ሺህ 744 የሚደርሱ የትምህርት ተቋማት አሉ፤ ከግብዓት አንጻር ደረጃቸውን የጠበቁት 4 ነጥብ 6 በመቶ ብቻ መሆናቸውም በውይይቱ ላይ ተነስቷል።

ከዚህ ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑትን በለውጥ እቅዱ መሠረት በሦስት ዓመታቱ መጨረሻ ደረጃቸውን ለማሻሻል ግብ ተጥሎ እየተሠራ እንደሆነም ታውቋል። ያልተሟላ የግብዓት አቅርቦት የሚታይባቸውንና በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኙትን የትምህርት ተቋማት ደረጃ ለማሻሻል ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም የውይይቱ ተሳታፊዎች አስታወቀዋል።

የአማራ ልማት ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፋንታን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል። አልማ በ1984 ዓ.ም ነበር በጥቂት በጎ አሳቢ ግለሰቦች የተመሠረተው። በአሁኑ ወቅት ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ አባላት አሉት።

ዘጋቢ፡-ኃይሉ ማሞ-ከጎንደር

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

The post በጎንደር ከተማ አስተዳደር የትምህርት ተቋማትን ደረጃ ወደ 50 በመቶ ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡ appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

Trending Articles