Quantcast
Channel: , Author at Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

በመዲናዋ ወንጀል እየተፈጸመ ነው በሚል የውጭ ሃገራት ዜጎች ጉዞ እንዳያደርጉ በሚል የተናፈሰው ዜና ነባራዊ ሁኔታውን ያለገናዘበ ነው –ፖሊስ

$
0
0

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወንጀል በስፋት እየተፈፀመ ስለሆነ የውጪ ሀገራት ዜጎች ወደ ተጠቀሱት ስፍራዎች ጉዞ እንዳያደርጉ በማለት በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የተናፈሰው ዜና የከተማዋን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ እንደሆነና የከተማችን የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ መሆኑንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ/ም አንድ የውጪ ሀገር ዜጋ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልን በመጎብኘት ላይ እንዳሉ ስድስት ግለሰቦች በስለትና በዱላ በማስፈራራት ሁለት ቀለበት፣ 2 ሞባይልና 4ሺ ብር ቢወሰዱባቸውም ፖሊስ ባደረገው ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ያላቸውን ተጠርጣሪዎች በመያዝ ወንጀል የተፈፀመባቸው የውጪ ሀገር ዜጋ ተጠርጣሪዎቹን በአካል ቀርበው በመለየት እንዲያረጋግጡ ቢጠየቁም በልዩ ልዩ ምክንያት ያልቀረቡና ፖሊስ ከአካባቢው ሌሎች ተጨማሪ ማስረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ስፍራው በጣም ሰፊ እና ሰዋራ በመሆኑ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችል የተፈፀመው የወንጀል ድርጊትም እየተጣራ መሆኑን አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ስለ አካባቢው የፀጥታ ሁኔታ ከኮሚሽኑ በቂ መረጃ ሳይጠይቁ በስማ በለው ያገኙትን መረጃ መነሻ በመድረግ የከተማችን ፀጥታ አስተማማኝ እንዳልሆነ በተለይ ደግሞ በእንጦጦ ፓርክ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ መንቀሳቀስ ስጋት እንደሆነ አድርገው መዘገባቸው ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ሊታረም ይገባል ብሏል፡፡

በቅርቡ የተከበረው የገና በዓል በሰላም መከበሩንና ከ12ሺህ በላይ ሰዎች የታደሙበት ታላቁ ሩጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁ የከተማዋን ሰላማዊነት ማሳያ ስለመሆኑ ኮሚሽኑ አስታውሶ÷ በተጠቀሱት ስፍራዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ በመሆኑ ሰዎች በጋራም ሆነ በግል ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Source link

The post በመዲናዋ ወንጀል እየተፈጸመ ነው በሚል የውጭ ሃገራት ዜጎች ጉዞ እንዳያደርጉ በሚል የተናፈሰው ዜና ነባራዊ ሁኔታውን ያለገናዘበ ነው – ፖሊስ appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

Trending Articles