Quantcast
Channel: , Author at Satenaw: Ethiopian News | Breaking News: Your right to know!
Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

አማራዎች በተገደሉባቸው ቀናቶች የተሰሙ ሰበር ዜናዎች….?!? (አሳዬ ደርቤ)

$
0
0

አማራዎች በተገደሉባቸው ቀናቶች የተሰሙ ሰበር ዜናዎች….?!?

አሳዬ ደርቤ

16 ዐማራዎች ወለጋ ሆሮጉድሩ ውስጥ የተገደሉ ቀን… ‹‹ወ/ሮ ኬርያ ተያዘች›› አሉን፡፡

መተከል ላይ 261 ንጹሐን ተገድለው በጅምላ የተቀበሩ እለት…. የደንቢዶሎ ነዋሪዎች ዱላ ይዘው ኦነግ ሸኔን ጫካ ውስጥ ሲፈልጉ መዋላቸውን እና በርካታ የትሕነግ መኮንኖች መያዛቸውን የሚገልጽ ዜና ቀረበልን፡፡

ኢሰማኮ በቤኒሻንጉል ክልል ‹‹ከመቶ የሚበልጡ ንጹሐን መገደላቸውን እና ከጥቃቱ በፊት መከላከያ ሠራዊቱ እንዲወጣ መደረጉን›› የገለጸ ቀን….. ‹‹ጃል መሮ ተገድሏል›› የሚል ሰበር ዜና ተነገረን፡፡

ኮንሶ ላይ 66 ዜጎች መገደላቸው የተሰማ እለት…. ‹‹ደብረ ጽዮን ተደመሰሰ›› የሚል የሐሰት ዜና ለቀቁብን፡፡

ሆሮ ጉድሩ ላይ 54 ንጹሐን ተጨፍጭፈው ያደሩ እለት…. በአል-ነጃሺ መስጂድ ላይ ጉዳት መድረሱን ከሚገልጽ ፎቶ ጋር እነ ሴኮ ቱሬ መደምሰሳቸውን ሰማን፡፡

ኢሰመኮ ‹‹መንግሥት ያለ አይመስልም ነበር›› የሚል መግለጫውን ያወጣ እለት …

በርካታ የትሕነግ ኮሎኔሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አበሰሩን፡፡

በሁለት ቀን ውስጥ መተከል ላይ ከ160 በላይ ንጹሐን የተጨፈጨፉ እለት ‹‹እነ አባይ ጸሐዬ ተደመሰሱ›› የሚል ሰበር ዜና ተነገረን፡፡

ምን ለማለት ፈልጌ ነው?

መተከል፣ ወለጋ- በደረሰ ጥቃት፤ እንደ ፋሲካ በግ

አማራ ሲታረድ- ባደረበት ማግሥት፤ መረጃው ሲወጣ- ፎቷቸው ሲለቀቅ፤ ፍትሕን ተውና

ሞቱን የሚያስረሳ- ሰበር ዜና ጠብቅ፡፡

ይህን ሁኔታ የተከታተለው ዶ/ር ሰማህኝ ጋሹም ይህን ብሏል

በእያንዳንዷ የአብይ ሰበር ዜና ውስጥ  በመቶ ሺ ዎች የሚቆጠር የአማራ  የታፈነ የዋይታ ድምጽ አለ…!!

Source link

The post አማራዎች በተገደሉባቸው ቀናቶች የተሰሙ ሰበር ዜናዎች….?!? (አሳዬ ደርቤ) appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 8076

Trending Articles